ነህምያ 10:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ሥርዐት በራሳችን ላይ እናደርጋለን። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 “በየዓመቱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት የሚሆን የሰቅል አንድ ሦስተኛ ለመስጠት ቃል እንገባለን፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 የምድሪቱ ሕዝቦች ሸቀጥ ወይም ልዩ ልዩ እህል ለመሸጥ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ በሰባተኛው ዓመትም ምድሪቱን እናሳርፋታለን፥ ዕዳንም ሁሉ እንሰርዛለን። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 በየዓመቱ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውል እያንዳንዳችን የጥሬ ብር አንድ ሦስተኛ እጅ በማምጣት እንሰጣለን። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32-33 ስለ አምላካችንም ቤት አገልግሎት፥ ስለ ገጸ ኅብስትም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቁርባንና ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት፥ ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ትእዛዝ በራሳችን ላይ አደረግን። ምዕራፉን ተመልከት |