ናሆም 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይነጕዳሉ፥ አደባባይም ይጋጫሉ፣ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይከንፋሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ሠረገሎች በአደባባይ ወዲያ ወዲህ ይከንፋሉ፤ በመንገዶችም ላይ ይርመሰመሳሉ፤ የሚንበለበል ፋና ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 የጦረኞቹ ጋሻ ቀልቶአል፥ ኃያላን ሰዎችም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱ በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፥ ጦሮቹም ይወዘወዛሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሠረገሎቹ በከፍተኛ ፍጥነት በመንገዶች ይሽቀዳደማሉ፤ በአደባባዩም ላይ ወዲያና ወዲህ ይጣደፋሉ፤ የሚንቦገቦግ ችቦም ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ። ምዕራፉን ተመልከት |