ናሆም 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፣ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፣ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ነነዌ ሆይ፤ አጥቂ መጥቶብሻል፤ ምሽግሽን ጠብቂ፤ መንገድሽን ሰልዪ፤ ወገብሽን ታጠቂ፤ ኀይልሽን ሁሉ አሰባስቢ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እነሆ፥ መልካም ዜና የሚያመጣ፥ ሰላምንም የሚያሰማ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ በዓሎችሽን አክብሪ፥ ስእለቶችሽን ክፈዪ፤ አጥፊው ፈጽሞ ተቆርጧልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንቺ በኩል አያልፍምና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ነነዌ ሆይ! አደጋ ጣይ መጥቶብሻል! ስለዚህ ምሽጎችሽን አጠናክሪ! አውራ መንገዱን ሁሉ ጠብቂ! ወገብሽን ታጠቂ! ኀይልሽንም ሁሉ አጠናክሪ! ምዕራፉን ተመልከት |