Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሚክያስ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአልና በማሮት የምትቀመጠው በጎነትን ትጠባበቃለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከመከራው መገላገልን በመሻት፣ በማሮት የሚኖሩ በሥቃይ ይወራጫሉ፤ እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በማሮት የምትቀመጠው መልካም ነገርን ትጠባበቃለችና፤ ነገር ግን ክፉ ነገር ከጌታ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የማሮት ሕዝብ “መልካም ነገር ይመጣልናል” ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። እግዚአብሔር ግን ጥፋትን በኢየሩሳሌም ላይ አውርዶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአልና በማሮት የምትቀመጠው በጎነትን ትጠባበቃለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚክያስ 1:12
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን በጎ ነገ​ርን በተ​ጠ​ባ​በ​ቅ​ኋት ጊዜ እነሆ ክፉ ቀኖች መጡ​ብኝ፤ ብር​ሃ​ንን ተስፋ አደ​ረ​ግሁ፥ ጨለ​ማም መጣ​ብኝ።


ብር​ሃ​ንን ፈጠ​ርሁ፤ ጨለ​ማ​ው​ንም ፈጠ​ርሁ፤ ሰላ​ም​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፋ​ት​ንም አመ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ያደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።


በውኑ ይሁ​ዳን ፈጽ​መህ ጥለ​ኸ​ዋ​ልን? ነፍ​ስ​ህስ ጽዮ​ንን ጠል​ታ​ታ​ለ​ችን? ስለ ምን መታ​ኸን? ፈው​ስስ ስለ ምን የለ​ንም? ስለ ምን ተስፋ አደ​ረ​ግን? ነገር ግን መል​ካም ነገር አል​ተ​ገ​ኘም፤ የፈ​ው​ስን ጊዜ ተስፋ አደ​ረ​ግን፤ ነገር ግን ድን​ጋጤ ሆነ።


ሰላ​ምን በተ​ስፋ ተጠ​ባ​በ​ቅን፤ ለይ​ቅ​ር​ታም ጊዜ መል​ካም ነገ​ርን አጣን፤ እነ​ሆም ድን​ጋጤ ሆነ።


ወይስ በከ​ተማ ውስጥ መለ​ከት ሲነፋ ሕዝቡ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ክፉ ነገር በከ​ተማ ላይ ይመ​ጣ​ልን?


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


እርስዋም፦ ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና ማራ በሉኝ እንጂ ኑኃሚን አትበሉኝ።


በመ​ጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ልቡ ተና​ውጦ ነበ​ርና በመ​ን​ገድ ዳር በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ይጠ​ባ​በቅ ነበር፤ ሰው​ዬ​ውም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተ​ማ​ዪቱ ሁሉ ተጭ​ዋ​ጭ​ዋ​ኸች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች