Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኢየሱስ ሐሳባቸውን ተረድቶ እንዲህ አለ፤ “ክፉ ነገር በልባችሁ ለምን ታስባላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ስለምን ይህን ክፉ ነገር በልባችሁ ታስባላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 9:4
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁል​ጊዜ በል​ባ​ቸው ዐመ​ፃን የሚ​መ​ክሩ፥ ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ ይከ​ብ​ቡ​ኛል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገ​ባል፥ ክፉ አሳ​ብ​ንም ታስ​ባ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፦


ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፤” እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።


እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆ “ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ፤” አላቸው።


ወዲያውም ኢየሱስ በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ በመንፈስ አውቆ እንዲህ አላቸው “በልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ?


እርሱ ግን የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ስዋ የም​ት​ለ​ያይ መን​ግ​ሥት ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ቤትም እርስ በርሱ ቢለ​ያይ ያ ቤት ይወ​ድ​ቃል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በል​ባ​ችሁ ምን ታስ​ባ​ላ​ችሁ?


እርሱ ግን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ያው​ቅ​ባ​ቸው ነበ​ርና እጁ የሰ​ለ​ለ​ች​ውን ሰው፥ “ተነ​ሥ​ተህ በመ​ካ​ከል ቁም” አለው፤ ተነ​ሥ​ቶም ቆመ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ስም​ዖን ሆይ፥ የም​ነ​ግ​ርህ ነገር አለኝ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ተና​ገር” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊጠ​ይ​ቁት እን​ደ​ሚሹ ዐውቆ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ” ስለ አል​ኋ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ነገር እርስ በር​ሳ​ችሁ ትመ​ራ​መ​ራ​ላ​ች​ሁን?


አሁን አንተ ሁሉን እን​ደ​ም​ታ​ውቅ፥ ማንም ሊነ​ግ​ርህ እን​ደ​ማ​ትሻ ዐወ​ቅን፤ በዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣህ እና​ም​ና​ለን።”


ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ ነገር እንደ አን​ጐ​ራ​ጐሩ በልቡ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ያሰ​ና​ክ​ላ​ች​ኋ​ልን?


ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ውስጥ የማ​ያ​ምኑ አሉ፤” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከጥ​ንት ጀምሮ የማ​ያ​ም​ኑ​በት እነ​ማን እንደ ሆኑ፥ የሚ​ያ​ሲ​ዘ​ውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበ​ርና።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ትፈ​ታ​ተ​ኑት ዘንድ እን​ዴት ተባ​በ​ራ​ችሁ? እነሆ፥ ባል​ሽን የቀ​በ​ሩት ሰዎች እግ​ሮች በበር ናቸው፤ አን​ቺ​ንም ይወ​ስ​ዱ​ሻል” አላት።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች