Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፤ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቍማዳ ማንም አያስቀምጥም፤ ይህ ከሆነ አቍማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቍማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ነገር ግን አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቍማዳ ይጨመራል፤ በዚህ ሁኔታ የወይን ጠጁና አቍማዳው በደኅና ተጠብቀው ይቈያሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በአሮጌ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖሩታል፤ ሁለቱም ይጠበቃሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እንዲሁም በአረጀ የውሃ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር ማንም የለም፤ ይህ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ተበላሽቶ ከጥቅም ውጪ ይሆናል። ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ማኖር ይገባል፤ በዚህም ዐይነት፥ ሁለቱም በደኅና ተጠብቀው ይኖራሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 9:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በተሃ ጠጅ እንደ ተሞ​ላና ሊቀ​ደድ እንደ ቀረበ አቁ​ማዳ፥ ወይም እንደ አን​ጥ​ረኛ ወናፍ እነሆ፥ አን​ጀቴ ሆነ።


በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።


ይህንም ሲነግራቸው አንድ መኰንን መጥቶ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” እያለ ሰገደለት።


በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።”


አዲስ ጠጅ​ንም በአ​ሮጌ ረዋት የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ ወይ​ኑም ይፈ​ስ​ሳል፤ ረዋ​ቱም ይቀ​ደ​ዳል።


ነገር ግን አዲ​ሱን ጠጅ በአ​ዲስ ረዋት ያደ​ር​ጉ​ታል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይጠ​ባ​በ​ቃሉ።


እነ​ርሱ ደግሞ ተን​ኰል አድ​ር​ገው መጡ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ስንቅ ያዙ፤ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ላይ አሮጌ ዓይ​በ​ትና ያረ​ጀና የተ​ቀ​ደደ የተ​ጠ​ቀ​መም የጠጅ ረዋት ተሸ​ከሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች