Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 9:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ ቍራጭ ጨርቅ የሚጥፍ ሰው የለም፤ ይህ ከሆነ አዲሱ ዕራፊ ካረጀው ልብስ ላይ ተቦጭቆ ቀዳዳውን የባሰ ያሰፋዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ ቀዳዳውም የባሰ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ ዕራፊ የሚጥፍ ማንም የለም፤ ቢጣፍ ግን አዲሱ ዕራፊ አሮጌውን ልብስ ቦጭቆ ቀዳዳውን የባሰ ያሰፋዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 9:16
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ብዙ ነገር ነበ​ረኝ፤ ነገር ግን አሁን ልት​ሸ​ከ​ሙት አት​ች​ሉም።


አሁ​ንም እነ​ዚህ ሦስቱ እም​ነት፥ ተስ​ፋና ፍቅር ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፤ ከሁሉ ግን ፍቅር ይበ​ል​ጣል።


ደስ​ተ​ኞ​ችም ሆን።


መን​ጋ​ውን እንደ እረኛ ያሰ​ማ​ራል፤ ጠቦ​ቶ​ቹን በክ​ንዱ ሰብ​ስቦ በብ​ብቱ ይሸ​ከ​ማል፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡ​ት​ንም በቀ​ስታ ይመ​ራል።


ጌታዬ ከአ​ገ​ል​ጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ዳ​ናም እን​ው​ላ​ለን፤ ወደ ጌታ​ችን ወደ ሴይር እስ​ክ​ን​ደ​ር​ስም በሕ​ፃ​ናቱ ርምጃ መጠን እን​ሄ​ዳ​ለን” አለው።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።


በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፤ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።”


በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።


ይህቺ የዚህ ሥራ አገ​ል​ግ​ሎት ግዳጅ የም​ት​ፈ​ጽ​መው ለዚህ ለቅ​ዱ​ሳን ችግር መሟ​ላት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ዱ​ሳን ዘን​ድም ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ታበ​ዛ​ለች።


በም​ሳ​ሌም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በአ​ሮጌ ልብስ ቀዳዳ ላይ የአ​ዲስ ልብስ እራፊ የሚ​ጥፍ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን አዲሱ አሮ​ጌ​ውን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ አዲሱ እራ​ፊም ከአ​ሮ​ጌው ጋር አይ​ስ​ማ​ማም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች