Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ፈሪሳውያንም ይህን ባዩ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ “መምህራችሁ ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኀጢአተኞች ጋራ ለምን ዐብሮ ይበላል?” ብለው ጠየቋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ፈሪሳውያንም ይህንን አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ለምን ይበላል?” አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ፈሪሳውያንም ይህን አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ስለምን አብሮ ይበላል?” አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን፦ መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 9:11
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።”


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ከቀ​ራ​ጮ​ችና ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ለምን ትበ​ላ​ላ​ችሁ? ትጠ​ጡ​ማ​ላ​ችሁ?” ብለው በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራ ጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው?” አሉ።


እርሱ ራሱም ደካማ ነውና ባለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው ከሳቱ ሰዎች ጋር መከ​ራን ሊቀ​በል ይች​ላል።


እኛ በት​ው​ል​ዳ​ችን አይ​ሁድ ነን፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች የሆኑ አሕ​ዛ​ብም አይ​ደ​ለ​ንም።


ሁሉም አይ​ተው “ወደ ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው ቤት ሊውል ገባ” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አት​ቅ​ረቡ” ይላሉ። ስለ​ዚ​ህም የቍ​ጣዬ ጢስ በዘ​መኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ።


“ወደ አል​ተ​ገ​ረ​ዙት ሰዎች ቤት ገብ​ተህ አብ​ረ​ሃ​ቸው በል​ተ​ሃል” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች