Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “ጌታ ሆይ!ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል” ብሎ ለመነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ጌታ ሆይ፤ ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ በመሠቃየት ከቤት ተኝቷል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ጌታ ሆይ! ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሠቃየ በቤት ተኝቶአል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “ጌታ ሆይ፥ አገልጋዬ ሽባ ሆኖ፥ እጅግ በመሠቃየት በቤት ተኝቶአል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል ብሎ ለመነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 8:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።


በዚ​ያም ኤንያ የተ​ሰኘ ሰውን አገኘ፤ እር​ሱም ታሞ በአ​ልጋ ከተኛ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበ​ርና።


ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም፤ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?


የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።


ያነ​ጋ​ገ​ረ​ውም መል​አክ ከሄደ በኋላ ከሎ​ሌ​ዎቹ ሁለት፥ ከማ​ይ​ለ​ዩት ጭፍ​ሮ​ቹም አንድ ደግ ወታ​ደር ጠራ።


ርኩ​ሳን መና​ፍ​ስት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ብዙ​ዎች ነበ​ሩና፥ በታ​ላቅ ቃል እየ​ጮኹ ይወጡ ነበር፤ ብዙ​ዎች ልም​ሾ​ዎ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ይፈ​ወሱ ነበር።


እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።


ኢየሱስም “እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች