Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ብዙ ሕዝብ እንደ ተሰበሰበ ባየ ጊዜ፣ ወደ ተራራ ወጣና ተቀመጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢየሱስ የሚከተለውን ብዙ ሕዝብ ባየ ጊዜ፥ ወደ ተራራ ወጥቶ ተቀመጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 5:1
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ተራራም ወጣ፤ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፤ ወደ እርሱም ሄዱ።


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ወደ ገሊላ ባሕር አጠገብ መጣ፤ ወደ ተራራም ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ።


ደግሞም በባሕር ዳር ሊያስተምር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ እርሱ በታንኳ ገብቶ በባሕር ላይ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕር ዳር በምድር ላይ ነበሩ።


ወደ ቤትም መጡ፤ እንጀራም መብላት ስንኳ እስኪሳናቸው ድረስ እንደ ገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ።


ከገሊላም ከዐሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።


እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር።


አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦


በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።


እር​ሱም ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ድሆች፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የእ​ና​ንተ ናትና።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ጴጥ​ሮ​ስን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዮሐ​ን​ስን ይዞ​አ​ቸው ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ነጥ​ቀው ሊያ​ነ​ግ​ሡት እን​ደ​ሚሹ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና ብቻ​ውን ወደ ተራራ ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች