Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እርሱም “በኋላዬ ኑ፤ ሰዎችንም አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ኢየሱስም፣ “ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እርሱም “ኑ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ኢየሱስም “ኑ ተከተሉኝ፤ ዓሣን እንደምታጠምዱ ሁሉ ሰዎችን እንድትሰበስቡልኝ አደርጋችኋለሁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 4:19
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ካለ ይከ​ተ​ለኝ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ እኔ ባለ​ሁ​በት በዚያ ይኖ​ራ​ልና፤ እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝ​ንም አብ ያከ​ብ​ረ​ዋል።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።


ሌላ​ው​ንም፥ “ተከ​ተ​ለኝ” አለው፤ እርሱ ግን፥ “አቤቱ፥ በፊት ሄጄ አባ​ቴን እን​ድ​ቀ​ብ​ረው ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እስ​ክ​መጣ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ፤ አንተ ግን ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


እር​ሱም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ወሰ​ደው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስም​ዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባ​ላ​ለህ፤” አለው፤ ትር​ጓ​ሜ​ውም ጴጥ​ሮስ ማለት ነው።


ከዚ​ህም በኋላ ከዚያ ወጥቶ ሌዊ የሚ​ባል ቀራጭ ሰው በቀ​ረጥ መቀ​በ​ያው ቦታ ተቀ​ምጦ አየና፥ “ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና “ተከተለኝ፤” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


ኢየሱስም “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ፤” አለው።


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


ኢየሱስ “ተከተለኝ፤ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤” አለው።


እኔ አል​ከ​በ​ድ​ሁ​ባ​ች​ሁም፤ ነገር ግን ምክር ዐዋቂ ሆኜ በመ​ጠ​በብ ወሰ​ድ​ኋ​ችሁ።


በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።


ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች