Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 28:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና “ደስ ይበላችሁ፤” አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ወዲያው ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢየሱስ በመንገድ አገኛቸውና “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ እርሱ ቀረቡና እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና፦ ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 28:9
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ።


በታንኳይቱም የነበሩት “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” ብለው ሰገዱለት።


ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ አም​ላ​ኬም” ብሎ መለሰ።


እነ​ር​ሱም ሰገ​ዱ​ለ​ትና በታ​ላቅ ደስታ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።


ማር​ያም ግን ዋጋዉ የከ​በ​ረና የበዛ አንድ ነጥር የጥሩ ናር​ዶስ ሽቱ ወሰ​ደ​ችና የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እግር ቀባ​ችው፤ በፀ​ጕ​ሯም አሸ​ችው፤ የዚያ ሽቱ መዓ​ዛም ቤቱን መላው።


በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም በእ​ግ​ሮቹ አጠ​ገብ ቆማ አለ​ቀ​ሰች፤ እግ​ሮ​ቹ​ንም በእ​ን​ባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕ​ር​ዋም እግ​ሮ​ቹን ታብ​ሰ​ውና ትስ​መው፥ ሽቱም ትቀ​ባው ነበር።


እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።


ወድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአ​ንድ ልብም ሁኑ፤ በሰ​ላም ኑሩ፤ የሰ​ላ​ምና የፍ​ቅር አም​ላ​ክም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን።


ያም ከሳ​ም​ንቱ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቤት ደጁ ተቈ​ልፎ ሳለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው።


መል​አ​ኩም ወደ እር​ስዋ ገብቶ፥ “ደስ ያለሽ፥ ጸጋ​ንም የተ​መ​ላሽ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ” አላት።


በቸ​ር​ነ​ትህ የሚ​ታ​ገሡ መን​ገ​ድ​ህ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ይገ​ና​ኙ​ሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈ​ጣህ፤ እኛም ኀጢ​አት ሠራን፤ ስለ​ዚ​ህም ተሳ​ሳ​ትን።


በገበያም ሰላምታና ‘መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!’ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።


እነሆም ነገርኋችሁ።” በፍርሃትና በታላቅ ደስታም ፈጥነው ከመቃብር ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊያወሩ ሮጡ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ፤ በዚያም ያዩኛል፤” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች