Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 28:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና፤ በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እርሱ በዚህ የለም፤ እንደ ተናገረው ተነሥቷል፤ ኑና ተኝቶበት የነበረውን ቦታ እዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዚህ የለም፤ እንደ ተናገረው ተነሥቶአልና፤ ተኝቶ የነበረበትን ስፍራ ኑና እዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እርሱ እዚህ የለም ቀደም ብሎ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል። እዚህ የለም፤ ተቀብሮበት የነበረበትን ስፍራ ኑና እዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 28:6
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።


ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።


በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው። እጅግም አዘኑ።


ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ፤” ብሎ አዘዛቸው።


ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።


“ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፤’ እንዳለ ትዝ አለን።


እርሱ ግን “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፤ በዚህ የለም፤ እነሆ፥ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።


የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊናቅ፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።


ጴጥ​ሮ​ስም ተነሣ፤ ወደ መቃ​ብ​ርም ፈጥኖ ሄደ፤ ዝቅ ብሎም በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ በፍ​ታ​ውን ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ አየ፤ የሆ​ነ​ው​ንም እያ​ደ​ነቀ ተመ​ለሰ።


ሥጋ​ው​ንም በአ​ላ​ገኙ ጊዜ ተመ​ል​ሰው፦ ተነ​ሥ​ቶ​አል ያሉ​አ​ቸ​ውን የመ​ላ​እ​ክ​ትን መልክ እንደ አዩ ነገ​ሩን።


እር​ሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነ​ቢ​ያ​ትና በመ​ዝ​ሙ​ርም ስለ እኔ የተ​ነ​ገ​ረው ይፈ​ጸም ዘንድ እን​ዳ​ለው፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም፤ አብ ይወ​ድ​ደ​ኛል፥ እንደ ገና አስ​ነ​ሣት ዘንድ እኔ ነፍ​ሴን እሰ​ጣ​ለ​ሁና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን ቤተ መቅ​ደስ አፍ​ር​ሱት፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን አነ​ሣ​ዋ​ለሁ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን የሞ​ትን ማሰ​ሪያ ፈቶ ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ሞት እር​ሱን ሊይ​ዘው አይ​ች​ል​ምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች