Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 27:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ነው፤ አሁን ከመስቀል ይውረድና እኛም በእርሱ እናምናለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እንመንበት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 27:42
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው።


“ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው፤” የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።


ያን የዳ​ነ​ውን ሰውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ በአ​ዩት ጊዜ የሚ​ሉ​ትን አጡ።


ቃሌን ሰምቶ የማ​ይ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እኔ የም​ፈ​ር​ድ​በት አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ዓለ​ምን ላድን እንጂ በዓ​ለም ልፈ​ር​ድ​በት አል​መ​ጣ​ሁ​ምና።


የዘ​ን​ባባ ዛፍ ዝን​ጣፊ ይዘው “ሆሣ​ዕና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት።


ዕውር የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰው ዳግ​መኛ ጠር​ተው፥ “ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና አቅ​ርብ፤ ይህ ሰው ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን” አሉት።


እን​ዲህ እያሉ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ቡሩክ ነው፤ ሰላም በም​ድር፥ በአ​ር​ያ​ምም ክብር ይሁን።”


“ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ፤” አሉት።


እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ


እንዲሁም የካህናት አለቆች ደግሞ ከጻፎች ጋር እርስ በርሳቸው እየተዘባበቱ “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤


አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤” አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር።


ሕዝ​ቡም ቆመው ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ አለ​ቆ​ችም፥ “ሌሎ​ችን አዳነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ክር​ስ​ቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌ​ዙ​በት ነበር።


እን​ዲ​ህም ይሉት ነበር፥ “አንተ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ከሆ​ን​ህስ ራስ​ህን አድን።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች