Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 26:65 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀድዶ፣ “በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ተናግሯል፤ ከዚህ ሌላ ምን ምስክርነት ያስፈልገናል? በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል መናገሩን እናንተው ራሳችሁ ሰምታችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህኑ ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ “ተሳድቦአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን መያዝ ለምን ያስፈልገናል? እነሆ አሁን ስድቡን ሰምታችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቃው በብስጭት ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ተናግሮአል! እናንተም ስድቡን ሰምታችኋል! ከዚህ የበለጠ ምን ምስክር ያስፈልጋል!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 26:65
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነኝ ብላ​ችሁ፥ አብ የቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ወደ ዓለ​ምም የላ​ከ​ውን እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ? ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ።


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ፥ ሰው ስት​ሆን ራስ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህና፤ ስለ መሳ​ደ​ብህ ነው እንጂ ስለ መል​ካም ሥራ​ህስ አን​ወ​ግ​ር​ህም” አሉት።


እነሆም ከጻፎቹ አንዳንዶቹ በልባቸው “ይህስ ይሳደባል፤” አሉ።


ንጉ​ሡም፥ ይህ​ንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ሁሉ አል​ደ​ነ​ገ​ጡም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አል​ቀ​ደ​ዱም።


ምድ​ሪ​ቱን ከሰ​ለ​ሉት ጋር የነ​በ​ሩት የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ፤


ሐዋ​ር​ያት በር​ና​ባ​ስና ጳው​ሎ​ስም በሰሙ ጊዜ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ፤ ፈጥ​ነ​ውም እየ​ጮኹ ወደ ሕዝቡ ሄዱ።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “የሚ​ሳ​ደብ ይህ ማን ነው? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ኀጢ​አ​ትን ማስ​ተ​ስ​ረይ ማን ይች​ላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።


የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊው ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገቡ፥ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


ወይም ጎባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዐይነ መጭ​ማጫ፥ ወይም ቅን​ድበ መላጣ፥ ወይም እከ​ካም፥ ወይም ቋቍ​ቻም፥ ወይም የአ​ባ​ለ​ዘሩ ፍሬ አንድ የሆነ ነው​ረኛ ሁሉ አይ​ቅ​ረብ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች