Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 25:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እርሱ ግን መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም፤’ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እርሱ ግን መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ አላውቃችሁም’ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሱ ግን ‘እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም’ ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እርሱ ግን፥ ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ እኔ አላውቃችሁም!’ ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 25:12
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ወድ ሰው ግን እርሱ በእ​ርሱ ዘንድ በእ​ው​ነት የታ​ወቀ ነው።


ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።


የእኔ የሆኑ በጎች ግን ቃሌን ይሰ​ሙ​ኛል፤ እኔም አው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይከ​ተ​ሉ​ኛል።


እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ራ​ው​ንና ፈቃ​ዱን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እር​ሱን ይሰ​ማ​ዋል እንጂ ኃጥ​ኣ​ንን እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


ዐመ​ፀ​ኞ​ችም በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት አይ​ኖ​ሩም፤ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ጠላህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ንን መን​ገድ ያው​ቃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣን መን​ገድ ግን ትጠ​ፋ​ለች።


ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐወ​ቃ​ች​ሁት፤ ይል​ቁ​ንም እርሱ ዐወ​ቃ​ችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደ​ዚያ ወደ ደካ​ማው፥ ወደ ድሀው ወደ​ዚህ ዓለም ጣዖት ተመ​ል​ሳ​ችሁ፥ ትገ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ዴት ፈጠ​ራን ትሻ​ላ​ችሁ?


ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?


በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን፤’ አሉ።


ቀኒቱንና ስዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።


ባለ​ቤቱ ተነ​ሥቶ ደጁን ይዘ​ጋ​ልና፤ ያን​ጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈ​ት​ልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀ​ም​ራሉ፤ መል​ሶም፦ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም ይላ​ቸ​ዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች