Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በሰማይ ያለ አንድ አባት ስላላችሁ፣ በምድር ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ፥ አባታችሁ አንድ እርሱም በሰማይ ያለው ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ደግሞም እናንተ ያላችሁ በሰማይ አንድ አባት ብቻ ስለ ሆነ በምድር ላይ ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 23:9
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።


በሥጋ የወ​ለ​ዱን አባ​ቶ​ቻ​ችን የሚ​ቀ​ጡን፥ እኛም የም​ን​ፈ​ራ​ቸው ከሆነ፥ እን​ግ​ዲያ ይል​ቁን ለመ​ን​ፈስ አባ​ታ​ችን ልን​ታ​ዘ​ዝና ልን​ገዛ በሕ​ይ​ወ​ትም ልን​ኖር እን​ዴት ይገ​ባን ይሆን?


እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።


እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው!


በክ​ር​ስ​ቶስ ብዙ መም​ህ​ራን ቢኖ​ሩ​አ​ች​ሁም አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ሉም፤ እኔ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በት​ም​ህ​ርት ወል​ጄ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


“እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ችና አባ​ቶች፥ አሁን በፊ​ታ​ችሁ የም​ና​ገ​ረ​ውን ስሙኝ።”


ኤል​ሳ​ዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ኀይ​ላ​ቸ​ውና ጽን​ዓ​ቸው፥” ብሎ ጮኸ። ከዚ​ያም ወዲያ ዳግ​መኛ አላ​የ​ውም፤ ልብ​ሱ​ንም ይዞ ከሁ​ለት ቀደ​ደው።


ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።


ኤል​ሳ​ዕም በሚ​ሞ​ት​በት በሽታ ታመመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለ​ቀ​ሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ባያ​ቸው ጊዜ ኤል​ሳ​ዕን፥ “አባቴ ሆይ፥ ልግ​ደ​ላ​ቸ​ውን?” አለው።


ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና ‘ሊቃውንት’ ተብላችሁ አትጠሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች