Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 22:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31-32 ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ስለ ሙታን ትንሣኤ ግን እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ የተናገራችሁን አላነበባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ እንዲህ ተብሎ የተነገረውን አላነበባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ደግሞ ስለ ሙታን መነሣት እግዚአብሔር ለእናንተ የነገራችሁን አላነበባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31-32 ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን፦ እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 22:31
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ግን እንዲህ አላቸው “ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት በተራቡ ጊዜ፥ እርሱ ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ ካህናትም ብቻ እንጂ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሊበሉት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕቱን ኅብስት እንደ በላ አላነበባችሁምን?


‘ምሕረትን እወዳለሁ፤ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኀጢአት የሌለባቸውን ባልኵኦነናችሁም ነበር።


“እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን?” አሉት። ኢየሱስም “እሰማለሁ፤ ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ፤’ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።


ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?


በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም።


ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች