Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 21:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እነርሱም፣ “እነዚያን ክፉዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ከወይኑ ዕርሻ ተገቢውን ፍሬ በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ሁኔታ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ሥፍራ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 እነርሱም “የእነዚህን ክፉ ሰዎች ፍጻሜ የከፋ ያደርገዋል። የወይኑንም ተክል ቦታ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እነርሱም፦ ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፥ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 21:41
38 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም በተ​ቃ​ወ​ሙ​ትና በሰ​ደ​ቡት ጊዜ ልብ​ሱን አራ​ግፎ፥ “እን​ግ​ዲህ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ደማ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ነው፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ወደ አሕ​ዛብ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች፤ ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።


እን​ግ​ዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገ​ኘች ይህቺ ድኅ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ እን​ደ​ም​ት​ሆን ዕወቁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ሙ​ታል።”


ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ?


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።


የፑ​ፕ​ል​ዮ​ስም አባት በን​ዳ​ድና በተ​ቅ​ማጥ ታሞ ተኝቶ ይኖር ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም እርሱ ወዳ​ለ​በት ገብቶ ጸለ​የ​ለት፤ እጁ​ንም በላዩ ጭኖ ፈወ​ሰው።


ብዙ ክር​ክ​ርም ከተ​ከ​ራ​ከሩ በኋላ ጴጥ​ሮስ ተነ​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአ​ሕ​ዛብ ከአፌ የወ​ን​ጌ​ሉን ቃል እን​ዳ​ሰ​ማ​ቸ​ውና እን​ዲ​ያ​ምኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ እንደ መረ​ጠኝ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።


ምድሪቱም ታለቅሳለች፣ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣


በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ።


የሚያፈራበትም ጊዜ ሲቀርብ፥ ፍሬውን ሊቀበሉ ባሮቹን ወደ ገበሬዎች ላከ።


እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል?”


የወ​ይኑ ባለ​ቤት በመጣ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል? ይመ​ጣል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ገባ​ሮች ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ኑ​ንም ለሌ​ሎች ገባ​ሮች ይሰ​ጣል፤” ቃሉ​ንም ሰም​ተው፥ “አይ​ሆ​ንም፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግም” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች