Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 21:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በማስተማር ላይ ሳለ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ቀርበው፣ “ይህን ሁሉ ነገር የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ሥልጣንስ የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ወደ መቅደስ ገብቶ በማስተማር ላይ ሳለ ሊቃነ ካህናትና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጥተው “እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ያስተምር ነበር። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ቀረቡና “ይህን ሁሉ የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና፦ በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 21:23
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው።


ዘወ​ት​ርም በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና የሕ​ዝብ ታላ​ላ​ቆ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


ወን​ድ​ሙን የሚ​በ​ድ​ለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አን​ተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደ​ረ​ገህ? ወይስ ግብ​ፃ​ዊ​ውን ትና​ንት እንደ ገደ​ል​ኸው ልት​ገ​ድ​ለኝ ትሻ​ለ​ህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእ​ው​ነት ይህ ነገር ታው​ቆ​አ​ልን?” ብሎ ፈራ።


ያም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን የሚ​በ​ድ​ለው ገፋው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦ ‘አን​ተን በእኛ ላይ ዳኛና ፈራጅ አድ​ርጎ ማን ሾመህ?


ኢየሱስም መልሶ “እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤


ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።


ከዚ​ህም በኋላ በአ​ንድ ቀን ሕዝ​ቡን በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው፥ ወን​ጌ​ል​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሡ​በት።


እነዚያንም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ፤ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ፤’ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች