Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 20:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” ብለው ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 በዚያም ሁለት ዐይነ ስውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ነበር፤ ኢየሱስም በዚያ ማለፉን ሲሰሙ፣ “ጌታ ሆይ፤ የዳዊት ልጅ ማረን!” በማለት ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እነሆ፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንደሚያልፍ በሰሙ ጊዜ “የዳዊት ልጅ፥ ጌታ ሆይ! ማረን” እያሉ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እነሆ፥ በመንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ዕውሮች በዚያ በኩል የሚያልፈው ኢየሱስ መሆኑን በሰሙ ጊዜ፥ “ጌታ የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረን!” እያሉ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን ብለው ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 20:30
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።


በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


ነቢይ ስለ ነበረ፥ ከአ​ብ​ራ​ኩም የተ​ገ​ኘ​ውን በዙ​ፋኑ እን​ዲ​ያ​ነ​ግ​ሥ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐ​ላን እንደ ማለ​ለት ስለ ዐወቀ፥


ያን​ጊ​ዜም ብዙ​ዎ​ችን ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውና ከሕ​መ​ማ​ቸው ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትም ፈወ​ሳ​ቸው፤ ለብ​ዙ​ዎች ዕው​ራ​ንም እን​ዲ​ያዩ ብር​ሃ​ንን ሰጣ​ቸው።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥


እነሆም ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል፤” ብላ ጮኸች።


እንደ ዕው​ሮች ወደ ቅጥሩ ተር​መ​ሰ​መሱ፤ ዐይ​ንም እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ተር​መ​ሰ​መሱ፤ በቀ​ት​ርም ጊዜ በመ​ን​ፈቀ ሌሊት እን​ዳለ ሰው ተሰ​ና​ከሉ፤ እንደ ሙታ​ንም ይጨ​ነ​ቃሉ።


እና​ንተ ደን​ቆ​ሮች፥ ስሙ፤ እና​ን​ተም ዕው​ሮች እዩ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም።


ዕው​ሮ​ች​ንም በማ​ያ​ው​ቋት መን​ገድ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ያ​ው​ቋ​ት​ንም ጎዳና እን​ዲ​ረ​ግጡ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ጠማ​ማ​ው​ንም አቀ​ና​ለሁ። ይህ​ንም አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምም።


በዚ​ያም ቀን ደን​ቆ​ሮች የመ​ጽ​ሐ​ፍን ቃል ይሰ​ማሉ፤ በጨ​ለ​ማና በጭ​ጋግ ውስ​ጥም የዕ​ው​ሮች ዐይ​ኖች ያያሉ።


ሰማ​ዩን በደ​መ​ናት የሚ​ሸ​ፍን፥ ለም​ድ​ርም ዝና​ምን የሚ​ያ​ዘ​ጋጅ፥ ሣርን በተ​ራ​ሮች ላይ፥ ልም​ላ​ሜ​ው​ንም ለሰው ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​በ​ቅል፥


እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፤ ወፎችም መጥተው በሉት።


ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” እያሉ አብዝተው ጮኹ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች