Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እርሱም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ኢየሱስም፣ “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንዱ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ከፈለግህ ግን ትእዛዞቹን ጠብቅ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሱም “ስለ መልካም ነገር እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ከፈልግህ ግን ትእዛዛቱን ጠብቅ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም፦ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 19:17
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ሙሴም “የኦ​ሪ​ትን ጽድቅ መሥ​ራ​ትን የፈ​ጸመ ሁሉ በእ​ርሱ ይጸ​ድ​ቅ​በ​ታል” አለ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ የለ​ምና፥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ የለ​ምና፤ አቤቱ፥ ከአ​ን​ተም በቀር ቅዱስ የለም።


እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።


ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ወደ ሕግ​ህም ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ህም፤ ሰውም ባደ​ረ​ገው ጊዜ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ፍር​ድ​ህን ተላ​ለፉ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ አል​ሰ​ሙ​ምም።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ሰነፍ በልቡ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም ይላል። ረከሱ፥ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጐሰ​ቈሉ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች