Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዐይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዐይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እንዲሁም ዐይንህ ለመሰናክል ምክንያት ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ጣለው፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዓይንህ ካሰናከለህ አውጥተህ ጣለው፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል፥ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዐይንህም ኃጢአት እንድትሠራ ቢያስትህ አውጥተህ ወዲያ ጣለው! ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ ዘለዓለም ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 18:9
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሀል።


እርሱም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ፤” አለው።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


ቀኝ ዐይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና።


ዐይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዐይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።


የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ እንደ እነ​ዚያ እንደ ካዱት እን​ዳ​ን​ወ​ድቅ፥ ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ገባ ዘንድ እን​ፋ​ጠን።


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች