Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 18:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 “ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ወንድሞቻችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ፣ የሰማዩ አባቴም እንደዚሁ ያደርግባችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ከእናንተም እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ የሰማዩ አባቴ ደግሞ እንዲሁ ያደርግባችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 “እንግዲህ እናንተም እያንዳንዳችሁ ወንድማችሁን ከልብ ይቅር ባትሉ በሰማይ ያለው አባቴም እንዲሁ ያደርግባችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 18:35
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል።


ድሃን እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጣራል፥ የሚሰማውም የለም።


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።


የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፣ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ።


በዚ​ህም ሁሉ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ ይሁዳ በሐ​ሰት እንጂ በፍ​ጹም ልብዋ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።


እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኀጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች