Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋበት፣ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን ለመፈለግ አይሄድምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን ሊፈልግ አይሄድምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እስቲ ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን አንዱን ለመፈለግ አይሄድምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 18:12
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን እረኛ ከበ​ጎቹ መካ​ከል የተ​ለ​የ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ፥ እን​ደ​ዚሁ በጎ​ችን እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የጠ​ፋ​ው​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የደ​ከ​መ​ው​ንም አጸ​ና​ለሁ፤ የወ​ፈ​ረ​ው​ንና የበ​ረ​ታ​ው​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ በፍ​ር​ድም እጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


እን​ግ​ዲህ ለአ​ሕ​ዛብ ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት አይ​በ​ሉ​አ​ቸ​ዋም፤ ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጣሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም።


በጎች በተ​ራ​ሮች ሁሉና በረ​ዘሙ ኮረ​ብ​ቶች ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ በጎ​ችም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ የሚ​ፈ​ል​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።


እርሱ ግን “ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?


“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነ​ዋል፤ እረ​ኞ​ቻ​ቸው አሳ​ቱ​አ​ቸው፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ የተ​ቅ​በ​ዘ​በዙ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ከተ​ራራ ወደ ኮረ​ብታ ዐለፉ፤ በረ​ታ​ቸ​ው​ንም ረሱ።


“ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ ‘ልጄ ሆይ! ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ፤’ አለው።


ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ደ​ሚ​ነ​ገር እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ው​ንም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቹም አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች አስ​ቀ​ድ​መው መጥ​ተው ለሶ​ርያ ንጉሥ ለወ​ልደ አዴር፥ “እነሆ፥ ሰዎች ከሰ​ማ​ርያ መጡ” ብለው ነገ​ሩት።


የደ​ከ​መ​ውን አላ​ጸ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የታ​መ​መ​ው​ንም አል​ፈ​ወ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የጠ​ፋ​ው​ንም አል​ፈ​ለ​ጋ​ች​ሁ​ትም፤ በኀ​ይ​ልና በጭ​ቈ​ናም ገዛ​ች​ኋ​ቸው።


ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች