Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 17:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በገሊላም ሲመላለሱ ኢየሱስ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፤ ይገድሉትማል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በገሊላ ተሰባስበው ሳሉ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ዐልፎ ይሰጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በገሊላ ተሰባስበው ሳሉ ኢየሱስ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ደቀ መዛሙርቱ በገሊላ በተሰበሰቡ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በገሊላም ሲመላለሱ ኢየሱስ፦ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፥ ይገድሉትማል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 17:22
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።


የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊናቅ፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።


በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው። እጅግም አዘኑ።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥


ክር​ስ​ቶስ እን​ዲህ ይሞት ዘንድ ወደ ክብ​ሩም ይመ​ለስ ዘንድ ያለው አይ​ደ​ለ​ምን?”


“ለሰው ልጅ ብዙ መከራ ያጸ​ኑ​በት ዘንድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችም ይፈ​ት​ኑት ዘንድ፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ፥ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነሣ ዘንድ አለው” አላ​ቸው።


አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከነ​ቢ​ያት ያላ​ሳ​ደ​ዱት ማን አለ? ዛሬም እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ የሰ​ጣ​ች​ሁ​ት​ንና የገ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን መም​ጣት አስ​ቀ​ድ​መው የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ተነሡ፤ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል፤” አላቸው።


በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤


እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።”


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተማ​ርሁ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እር​ሱን ራሱን በያ​ዙ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ኅብ​ስ​ቱን አነሣ።


ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።


ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ፤” ብሎ አዘዛቸው።


ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው፤” አላቸው።


እነ​ር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ባደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ሁሉ ሲደ​ነቁ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች