Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ኢየሱስም፣ “ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠበቁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ልብ አድርጉ፤ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኢየሱስም፦ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 16:6
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እስ​ኪ​ረ​ጋ​ገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ ተጠ​በቁ፤ ይኸ​ውም ግብ​ዝ​ነት ነው።


ጥቂት እርሾ ብዙ​ውን ዱቄት መጻጻ ያደ​ር​ገው የለ​ምን?


እርሱም “ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ፤” ብሎ አዘዛቸው።


እነርሱም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ እርሾ አይ​ሁ​ን​በት፤ እርሾ ያለ​በት ነገር፥ ማርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ይሆን ዘንድ አታ​ቀ​ር​ቡ​ምና።


“ዕወቁ፤ ከቅ​ሚ​ያም ሁሉ ተጠ​በቁ፤ ሰው የሚ​ድን ገን​ዘብ በማ​ብ​ዛት አይ​ደ​ለ​ምና” አላ​ቸው።


ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?


ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።


ደቀ መዛሙርቱም ወደ ማዶ በመጡ ጊዜ እንጀራ መያዝን ረሱ።


እነርሱም “እንጀራ ባንይዝ ነው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።


ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንድትጠበቁ ብዬ ስለ እንጀራ እንዳልተናገርኋችሁ እንዴት አታስተውሉም?”


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “አን​ዳች የሚ​በ​ላው ምግብ ያመ​ጣ​ለት ሰው ይኖር ይሆን?” ተባ​ባሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች