Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 16:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ምስጉን ነህ፤ ይህን የገለጠልህ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! ይህን የገለጠልህ በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሰው አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 16:17
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልጆ​ች​ሽም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ፤ ልጆ​ች​ሽም በብዙ ሰላም ይኖ​ራሉ።


እኔ ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ደ​ክም ስለ እና​ንተ ጸለ​ይሁ፤ አን​ተም ተመ​ል​ሰህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አጽ​ና​ቸው።”


እር​ሱም መጀ​መ​ሪያ ወን​ድሙ ስም​ዖ​ንን አግ​ኝቶ “በት​ር​ጓ​ሜው ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲ​ሕን አገ​ኘ​ነው” አለው።


‘ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ’ ተብሎ በነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል፤ እን​ግ​ዲህ ከአ​ባቴ የሰማ ሁሉ ተምሮ ወደ እኔ ይመ​ጣል።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህን እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን፦ ሥጋ​ዊና ደማዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አይ​ወ​ር​ስም፥ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን አይ​ወ​ር​ስም።


በስ​ሙም ለአ​ሕ​ዛብ ወን​ጌ​ልን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ ልጁን ገለ​ጠ​ልኝ፤ ያን​ጊ​ዜም ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ሰው ጋር አል​ተ​ማ​ከ​ር​ሁም።


አም​ነን በጸ​ጋው ድነ​ና​ልና፤ ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ነው እንጂ የእ​ና​ንተ ሥራ አይ​ደ​ለም።


በሌላ ዘመን ለሰው ልጆች ያል​ተ​ገ​ለጠ ዛሬ ለቅ​ዱ​ሳን ሐዋ​ር​ያ​ቱና ለነ​ቢ​ያቱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እንደ ተገ​ለጠ፥


ሰል​ፋ​ችሁ፦ ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና።


ልጆች በሥ​ጋና በደም አንድ ናቸ​ውና፤ እርሱ ደግሞ በዚህ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እንደ ወን​ድም ሆነ​ላ​ቸው፤ መል​አከ ሞትን በሞቱ ይሽ​ረው ዘንድ፥ ይኸ​ውም ሰይ​ጣን ነው።


እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች