Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 15:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እርስዋ ግን መጥታ “ጌታ ሆይ! እርዳኝ፤” እያለች ሰገደችለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሴትዮዋም እግሩ ላይ ወድቃ፣ “ጌታ ሆይ፤ ርዳኝ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሷ ግን መጥታ እየሰገደች “ጌታ ሆይ! እርዳኝ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሴትዮዋ ግን ቀርባ በእግሩ ሥር ተንበረከከችና “ጌታ ሆይ! እባክህ እርዳኝ!” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 15:25
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው።


በማ​ኅ​ፀን ውስጥ ወን​ድ​ሙን በተ​ረ​ከዙ ያዘው፤ በደ​ካ​ማ​ነ​ቱም ጊዜ ከአ​ም​ላክ ጋር ታገለ።


በታንኳይቱም የነበሩት “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” ብለው ሰገዱለት።


እርሱ ግን መልሶ “የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም፤” አለ።


ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” እያሉ አብዝተው ጮኹ።


እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ “ጌታ ሆይ! ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” እያለ ሰገደለት።


ብዙ ጊዜም ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውኀም ጣለው፤ ቢቻልህ ግን እዘንልን፤ እርዳንም፤” አለው።


ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ “አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው፤” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች