Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና እንዲህ አሉት፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ፥ ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 15:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ታላቅ ውካ​ታም ሆነ፤ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ወገን የሆኑ ጸሐ​ፍት ተነ​ሥ​ተው ይጣ​ሉና ይከ​ራ​ከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ነው ክፉ ነገር የለም፤ መን​ፈስ ወይም መል​አክ ተና​ግ​ሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አን​ጣላ” አሉ።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ከቀ​ራ​ጮ​ችና ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ለምን ትበ​ላ​ላ​ችሁ? ትጠ​ጡ​ማ​ላ​ችሁ?” ብለው በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “የሚ​ሳ​ደብ ይህ ማን ነው? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ኀጢ​አ​ትን ማስ​ተ​ስ​ረይ ማን ይች​ላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።


ከዚ​ህም በኋላ፥ ከዕ​ለ​ታት በአ​ንድ ቀን ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው እን​ዲህ ሆነ፤ ከገ​ሊ​ላና ከይ​ሁዳ መን​ደ​ሮች፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የመጡ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የኦ​ሪት መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እር​ሱም ይፈ​ውስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነበረ።


ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም “ብዔል ዜቡል አለበት፤” ደግሞ “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” ብለው ተናገሩ።


“ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።


እላችኋለሁና ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።


አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የወ​ረዱ አይ​ሁድ ከብ​በ​ውት ቆሙ፤ ሊረቱ በማ​ይ​ች​ሉ​በ​ትም ብዙና ከባድ ክስ ከሰ​ሱት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች