Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ጴጥሮስም መልሶ “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንህ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ከሆንህስ፣ በውሃው ላይ እየተራመድሁ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንህ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ፥ “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንክ በባሕሩ ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ጴጥሮስም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 14:28
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም የሕ​ይ​ወት ቃል እያ​ለህ ወደ ማን እን​ሄ​ዳ​ለን?


በተ​ሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ሁላ​ች​ሁም እን​ዳ​ት​ታ​በዩ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ራሳ​ች​ሁን ከዝ​ሙት የም​ታ​ነ​ጹ​በ​ትን ዐስቡ እንጂ ትዕ​ቢ​ትን አታ​ስቡ፤ ሁሉም እንደ እም​ነቱ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ይኑር።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?” አለው።


እርሱም ቃሉን አበርትቶ “ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም፤” አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።


ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።


እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውሃው ላይ ሄደ።


ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች