Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 13:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ኢየሱስም ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ በዕርሻው ቦታ ጥሩ ዘር የዘራን ሰው ትመስላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት በእርሻው ላይ መልካም ዘርን የዘራ ሰውን ትመስላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እንዲሁም ኢየሱስ እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ በእርሻው መልካም ዘር የዘራውን ሰው ትመስላለች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 13:24
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕማ​ምን በሕ​ማም ላይ፥ ተስ​ፋ​ንም በተ​ስፋ ላይ ተቀ​በሉ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።


ስለ​ዚህ ሄደው ወደ ኋላ እን​ዲ​ወ​ድቁ፥ እን​ዲ​ሰ​በ​ሩም፥ ተጠ​ም​ደ​ውም እን​ዲ​ቸ​ገሩ፥ የግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃሉ በሕ​ማም ላይ ሕማም፥ በተ​ስፋ ላይ ተስፋ፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ምሳሌ መስ​ለህ ንገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦


የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፤ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።


ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።


ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤


ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው “መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤


“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዐይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤


“ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች።


“መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና።


“ሌላ ምሳሌ ስሙ። የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፤ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።


“መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች።


“በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ ዐሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።


ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።


በዚያ ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መን​ግ​ሥተ ሰማ​ያት ምን ትመ​ስ​ላ​ለች? በም​ንስ እመ​ስ​ላ​ታ​ለሁ?


ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት በምን እመ​ስ​ላ​ታ​ለሁ?


የእ​ው​ነት ቃል በሆ​ነው በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት፥ አስ​ቀ​ድሞ ስለ ሰማ​ች​ሁት፥ በሰ​ማይ ስለ ተዘ​ጋ​ጀ​ላ​ችሁ ተስ​ፋ​ች​ሁም እን​ጸ​ል​ያ​ለን።


ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች