Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 12:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 “ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ አያገኝምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 “ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ የሚሻውን ዕረፍት ግን አያገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 “ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ አያገኝምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ የሚያርፍበት ቦታ በመፈለግ ውሃ በሌለበት በደረቅ ቦታ ይዞራል። ነገር ግን አያገኝም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 12:43
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆም “ኢየሱስ ሆይ! የእግዚአብሔር ልጅ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?” እያሉ ጮኹ።


በተ​ራ​ሮች ላይ ወን​ዞ​ችን፥ በሸ​ለ​ቆ​ችም መካ​ከል ምን​ጮ​ችን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መቆ​ሚያ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ው​ንም ምድር ለውኃ መፍ​ለ​ቂያ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ሰይ​ጣ​ንም፥ “ከሰ​ማይ በታች በም​ድር ላይ ዞርሁ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ተመ​ላ​ለ​ስሁ” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መለሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ሰይ​ጣ​ንም፥ “ምድ​ርን ሁሉ ዞር​ሁ​አት፥ ከሰ​ማይ በታ​ችም ተመ​ላ​ለ​ስ​ሁና መጣሁ።” ብሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መለሰ።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤


ሲሞ​ንም ወዲ​ያ​ውኑ አምኖ ተጠ​መቀ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም ይከ​ተል ጀመር፤ በፊ​ል​ጶ​ስም እጅ የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደ​ነቅ ነበር።


አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


በዚያን ጊዜም ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ፤’ ይላል፤ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች