Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 12:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 መልካም ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር መልካም ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ካከማቸው ክፉ ነገር መጥፎ ነገርን ያወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 መልካም ሰው ከመልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 “መልካም ሰው ከመልካም መዝገቡ፥ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገቡ ክፉ ነገርን ያወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 12:35
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ልሱ ታውቁ ዘንድ ንግ​ግ​ራ​ችሁ ሁል​ጊዜ በጨው እንደ ተቀ​መመ በጸጋ ይሁን።


የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።


ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የሚጠብቀው ግን የዕውቀት መንፈስን ይሞላል።


በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ።


እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።


የሚ​ሰ​ሙ​አ​ችሁ ሞገ​ስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳ​ጃ​ችሁ እን​ዲ​ፈ​ጸም መል​ካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።


ክፉ ሰው ግን ምክርን አይሰማትም፤ ለማኅበሩም መልካምና መጥፎ ነው የሚለው የለም።


የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው። የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።


እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።


እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፤ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።


መል​ካም ሰው ከልቡ መል​ካም መዝ​ገብ መል​ካ​ምን ያወ​ጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝ​ገብ ክፉ ነገ​ርን ያወ​ጣል፤ ከልብ የተ​ረ​ፈ​ውን አፍ ይና​ገ​ራ​ልና።


እነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ህና የሚ​ነ​ግ​ሩህ፥ ቃል​ንም ከል​ባ​ቸው የሚ​ያ​ወጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች