Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 12:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እናንተ የእፉኝት ልጆች፤ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ መልካም ነገር መናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ የሞላውን አንደበት ይናገረዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ነገር ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ የሞላውን አፍ ይናገራልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እናንተ የእባብ ልጆች! ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ነገር መናገር እንዴት ትችላላችሁ? ሰው በአፉ የሚናገረው በልቡ ሞልቶ የተረፈውን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 12:34
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ በስ​ምህ አድ​ነኝ፥ በኀ​ይ​ል​ህም ፍረ​ድ​ልኝ።


የዐ​መ​ፀ​ኞች ነገር በረ​ታ​ብን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንስ አንተ ይቅር ትላ​ለህ።


ቤተ መቅ​ደ​ስህ ቅዱስ ነው በጽ​ድ​ቅም ድንቅ ነው። በም​ድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስ​ፋ​ቸው የሆ​ንህ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኃ​ኒ​ታ​ችን ሆይ ስማን።


የጠቢብ ልብ ከአፉ ይታወቃል፥ በከንፈሩም ዕውቀትን ይለብሳል።


ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።


ሰነፍ ግን ስን​ፍ​ናን ይና​ገ​ራል፤ ልቡም ዐመ​ፅን ያደ​ርግ ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስሕ​ተ​ትን ይና​ገር ዘንድ፥ የተ​ራ​በ​ች​ው​ንም ሰው​ነት ይበ​ትን ዘንድ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ንም ነፍስ ባዶ ያደ​ርግ ዘንድ ከን​ቱን ያስ​ባል።


ፍር​ድን ከመ​ከ​ተል ወደ ኋላ ርቀ​ናል፤ ጽድ​ቅም በሩቅ ቆሞ​አል፤ እው​ነ​ትም ከመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ታጥ​ቶ​አል፤ በቀና መን​ገ​ድም መሄድ አል​ቻ​ሉም።


ጽድ​ቅን የሚ​ና​ገር በእ​ው​ነ​ትም የሚ​ፈ​ርድ የለም፤ በከ​ንቱ ነገር ታም​ነ​ዋል፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ተና​ግ​ረ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ትን ፀን​ሰ​ዋል፤ በደ​ል​ንም ወል​ደ​ዋል።


ሰው ሁሉ ክፉና በደ​ለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመ​ፅን ይና​ገ​ራ​ልና፥ ስለ​ዚህ ጌታ በጐ​ል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ደስ አይ​ለ​ውም፤ ለሙት ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ራ​ራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።


ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው።


እናንተ እባቦች! የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?


ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?


ዮሐ​ን​ስም ሊያ​ጠ​ም​ቃ​ቸው የመ​ጡ​ትን ሰዎች እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ፉ​ኝት ልጆች፥ ከሚ​መ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ታመ​ልጡ ዘንድ ማን ነገ​ራ​ችሁ?


መል​ካም ሰው ከልቡ መል​ካም መዝ​ገብ መል​ካ​ምን ያወ​ጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝ​ገብ ክፉ ነገ​ርን ያወ​ጣል፤ ከልብ የተ​ረ​ፈ​ውን አፍ ይና​ገ​ራ​ልና።


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


የሚ​ሰ​ሙ​አ​ችሁ ሞገ​ስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳ​ጃ​ችሁ እን​ዲ​ፈ​ጸም መል​ካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።


የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነገ​ርም፥ የስ​ን​ፍና ነገ​ርም፥ ወይም የማ​ይ​ገባ የዋዛ ነገር በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ሁን፤ ማመ​ስ​ገን ይሁን እንጂ።


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።


እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ይበ​ቀ​ል​ልኝ፤ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች