Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 12:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ወይስ አንድ ሰው ወደ ኀይለኛ ሰው ቤት ገብቶ ንብረቱን ለመዝረፍ ቢፈልግ፣ አስቀድሞ ያን ኀይለኛ ሰው ሳያስር እንዴት አድርጎ ይሳካለታል? ኋላም ቤቱን መበዝበዝ ይችላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ወይስ አንድ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ንብረቱን እንዴት መዝረፍ ይችላል? ካሰረው በኋላ ግን ቤቱን ይዘርፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ደግሞስ አንድ ሰው አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ ንብረቱን መዝረፍ እንዴት ይችላል? ኀይለኛውን ካሰረው በኋላ ግን በእርግጥ ንብረቱን ሊዘርፍ ይችላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 12:29
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በውኑ ምር​ኮን ከኀ​ይ​ለኛ እጅ መቀ​ማት ይቻ​ላ​ልን? በግፍ የተ​ማ​ረ​ከስ ይድ​ና​ልን?


ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።


ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።


ነገር ግን አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፤ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።


ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።


ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች