Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ባማረ ልብስ ያጌጠ ሰው? ባማረ ልብስ ያጌጡ በነገሥታት ቤት አሉላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 11:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ።


በዚያም ቀን ነቢያቱ ሁሉ ትንቢትን ሲናገሩ እያንዳንዱ ስለ ራእዩ ያፍራል፣ ያታልሉም ዘንድ የማቅ ልብስ አይለብሱም።


በዚያ ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሞ​ጽን ልጅ ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “ሂድ፥ ማቅ​ህን ከወ​ገ​ብህ አውጣ፤ ጫማ​ህ​ንም ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ፤ ያለ​ጫ​ማም በባዶ እግ​ርህ ሂድ” ብሎ ተና​ገ​ረው። እን​ዲ​ህም አደ​ረገ፤ ራቁ​ቱ​ንም ያለ ጫማ ሄደ።


እነ​ር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ጠጕ​ራም ነው፤ በወ​ገ​ቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። እር​ሱም፥ “ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ ነው” አላ​ቸው።


ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”


በድ​ካ​ምና በጥ​ረት፥ ብዙ ጊዜም ዕን​ቅ​ልፍ በማ​ጣት፥ በመ​ራ​ብና በመ​ጠ​ማት፥ አብ​ዝ​ቶም በመ​ጾም፥ በብ​ር​ድና በመ​ራ​ቆት ተቸ​ገ​ርሁ።


እኛ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ እን​ራ​ባ​ለን፤ እን​ጠ​ማ​ለን፤ እን​ራ​ቈ​ታ​ለን፤ እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ማረ​ፊ​ያም የለ​ንም፤ እን​ደ​በ​ደ​ባ​ለ​ንም።


በአ​ንተ ዘንድ የተ​ደ​ላ​ደ​ለና የተ​ቀ​ማ​ጠለ ሰው በወ​ን​ድሙ፥ አብ​ራ​ውም በም​ት​ተኛ በሚ​ስቱ፥ በቀ​ሩ​ትም ልጆቹ ይቀ​ናል፤


እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ?


ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።


ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ቀጭን ልብስ የለ​በ​ሰ​ውን ሰው ነውን? እነሆ፥ በክ​ብር ልብስ ያጌ​ጡስ በነ​ገ​ሥ​ታት ቤት አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች