Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ‘እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲህ ተብሎ የተጻፈለት እርሱ ነው፤ “ ‘መንገድህን በፊትህ የሚያዘጋጅ፣ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤” ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እርሱ ‘እነሆ፥ እፊት እፊትህ እየሄደ፥ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ በፊት እልካለሁ’ ተብሎ የተጻፈለት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 11:10
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የዐ​ዋጅ ነጋሪ ቃል በም​ድረ በዳ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ጎዳና በበ​ረሃ አስ​ተ​ካ​ክሉ።


እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።


“እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ፤’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥


እር​ሱም፥ “ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ እያለ በም​ድረ በዳ የሚ​ሰ​ብክ የዐ​ዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” አለ።


በነቢዩ በኢሳይያስ “ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ” የተባለለት ይህ ነውና።


“የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” አለው።


ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።


አን​ተም ሕፃን፥ የል​ዑል ነቢይ ትባ​ላ​ለህ፤ መን​ገ​ዱን ትጠ​ርግ ዘንድ በፊቱ ትሄ​ዳ​ለ​ህና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች