Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ለመንገዳችሁም ከረጢት፣ ትርፍ እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ የዕለት ጕርሱ ይገባዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለመንገዳችሁ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ለሠራተኛ ምግቡ የሚገባው ስለ ሆነ ለመንገዳችሁ ከረጢት፥ ትርፍ እጀ ጠባብ፥ ትርፍ ጫማ፥ በትርም አትያዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 10:10
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ን​ተም ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁም፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ የማ​ገ​ል​ገ​ላ​ችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።


በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።


ለመንገድም ከበትር በቀር እንጀራም ቢሆን ከረጢትም ቢሆን መሐለቅም በመቀነታቸው ቢሆን እንዳይዙ አዘዛቸው።


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሁለት ልብስ ያለው አን​ዱን ለሌ​ለው ይስጥ፤ ምግብ ያለ​ውም እን​ዲሁ ያድ​ርግ።”


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በት​ርም ቢሆን፥ ከረ​ጢ​ትም ቢሆን፥ እን​ጀ​ራም ቢሆን፥ ወር​ቅም ቢሆን፥ ሁለት ልብ​ስም ቢሆን ለመ​ን​ገድ ምንም አት​ያዙ።


ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ።


ዳዊ​ትም በት​ሩን በእጁ ያዘ፤ ከወ​ን​ዝም አም​ስት ድብ​ል​ብል ድን​ጋ​ዮ​ችን መረጠ፤ በእ​ረኛ ኮሮ​ጆ​ውም በኪሱ ከተ​ታ​ቸው፤ ወን​ጭ​ፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ቀረበ።


ሳኦ​ልም አብ​ሮት ያለ​ውን ብላ​ቴና፥ “እነሆ! እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ምን እን​ወ​ስ​ድ​ለ​ታ​ለን? እን​ጀራ ከከ​ረ​ጢ​ታ​ችን አል​ቆ​አ​ልና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የም​ን​ወ​ስ​ድ​ለት ምንም የለ​ንም” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች