Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፤ አልቻሉምም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በተነሣበት ጊዜ ሁሉ ይጥለዋል፤ ዐረፋ ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ሰውነቱም ይደርቃል፤ ርኩስ መንፈሱን እንዲያስወጡት ደቀ መዛሙርትህን ጠየቅኋቸው፤ እነርሱ ግን አልቻሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በተነሣበት ጊዜ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋ ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፏጫል፤ ሰውነቱም ይደርቃል፤ ርኩስ መንፈሱን እንዲያስወጡት ደቀ መዛሙርትህን ጠየቅኋቸው፤ እነርሱ ግን አልቻሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በሚነሣበትም ጊዜ ይጥለዋል፤ አፉም ዐረፋ እየደፈቀ ጥርሶቹን ያፋጫል፤ ሰውነቱም ደርቆ እንደ በድን ይሆናል፤ ርኩሱንም መንፈስ እንዲያስወጡለት ደቀ መዛሙርትህን ጠይቄአቸው ነበር፤ ነገር ግን አልቻሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፥ ጥርሱንም ያፋጫል ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፥ አልቻሉምም አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 9:18
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል።


ጮኾም እጅግም አንፈራግጦት ወጣ፤ ብዙዎችም “ሞተ” እስኪሉ ድረስ እንደ ሙት ሆነ።


ወደ እርሱም አመጡት። እርሱንም ባየ ጊዜ ያ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠው፤ ወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ።


ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው፤” አለው።


ይህ​ንም ሰም​ተው ተበ​ሳጩ፤ ልባ​ቸ​ውም ተና​ደደ፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም አፋ​ጩ​በት።


የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


እነሆም ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል፤” ብላ ጮኸች።


የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


ሐሰ​ቴም በእኔ ላይ ተነ​ሣች፤ በፊ​ቴም ተከ​ራ​ከ​ረ​ች​ብኝ።


ከሕዝቡ አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ! ድዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼአለሁ፤


እርሱም መልሶ “የማታምን ትውልድ ሆይ! እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት፤” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች