Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ፈሪሳውያንና አይሁድ ሁሉ የአባቶችን ወግ ለመጠበቅ ሲሉ፣ በሥርዐቱ መሠረት እጃቸውን በጥንቃቄ ሳይታጠቡ አይበሉም ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ፈሪሳውያንና አይሁድ ሁሉ የአባቶችን ወግ ለመጠበቅ ሲሉ፥ በሥርዓቱ መሠረት እጃቸውን በጥንቃቄ ሳይታጠቡ አይበሉም ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ፈሪሳውያንና የቀሩትም አይሁድ የሽማግሌዎችን ወግ በመጠበቅ እጃቸውን በሥርዓቱ ካልታጠቡ አይበሉም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 7:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።”


ፈሪሳውያንና ጻፎችም “ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ፤” ብለው ጠየቁት።


ፈሪ​ሳ​ዊ​ዉም አይቶ አደ​ነቀ፤ ምሳ ለመ​ብ​ላት እጁን አል​ታ​ጠ​በም ነበ​ርና።


በዚ​ያም እንደ አይ​ሁድ ልማድ የሚ​ያ​ነ​ጹ​ባ​ቸው ስድ​ስት የድ​ን​ጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁለት ወይም ሦስት እን​ስራ ይይዙ ነበር።


ለአ​ባ​ቶች ሥር​ዐት እጅግ ቀና​ተኛ ነበ​ር​ሁና በወ​ገ​ኖች ዘንድ ከጓ​ደ​ኞች ሁሉ በአ​ይ​ሁድ ዘንድ እጅግ ከበ​ርሁ።


ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።


ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች