Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 16:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ወጥተው፣ በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋራ ይሠራ ነበር፤ ትምህርታቸውንም ተከትለው በሚፈጸሙ ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።]

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከዚያም ደቀመዛሙርቱ ወጥተው፥ በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ ትምህርታቸውንም ተከትለው በሚፈጸሙ ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ደቀ መዛሙርቱም በየስፍራው ሁሉ እየሄዱ አስተማሩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር። ተአምራትንም የማድረግ ሥልጣን በመስጠት የትምህርታቸውን እውነተኛነት ያጸና ነበር።]

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 16:20
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


በእኛ ዘንድ የተ​ፈ​ጸ​መ​ው​ንና የታ​መ​ነ​ውን የሥ​ራ​ውን ዜና በሥ​ር​ዐት ሊጽፉ የጀ​መሩ ብዙ​ዎች ናቸው።


ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤


በጌ​ታም ፊት ደፍ​ረው እያ​ስ​ተ​ማሩ፥ እር​ሱም የጸ​ጋ​ውን ቃል ምስ​ክር እያ​ሳ​የ​ላ​ቸው፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ድንቅ ሥራና ተአ​ም​ራ​ትን እያ​ደ​ረ​ገ​ላ​ቸው ብዙ ወራት ኖሩ።


በቅ​ዱሱ ልጅ​ህም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ሕሙ​ማ​ንን ትፈ​ውስ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራ​ንም ታደ​ርግ ዘንድ እጅ​ህን ዘርጋ።”


በሐ​ዋ​ር​ያት እጅም በሕ​ዝቡ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ​ዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም በሰ​ሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ በአ​ን​ድ​ነት ነበሩ።


በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


ከእ​ር​ሱም ጋር አብ​ረን እየ​ሠ​ራን፥ የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጓት እን​ማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለን።


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ጸጋ በመ​ስ​ጠት፥ በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአ​ም​ራ​ትም መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም አስ​ረ​ዳ​ላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች