Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 12:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር ‘እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ስለ ሙታን መነሣት ግን፣ በሙሴ መጽሐፍ ይኸውም ስለ ቍጥቋጦው በተነገረው ክፍል፣ እግዚአብሔር ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ ያለውን አላነበባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለ ሙታን ግን እንደሚነሡ እግዚአብሔር “እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤” እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቁጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለ ሙታን መነሣት የሆነ እንደ ሆነ ግን እግዚአብሔር ሙሴን ከቊጥቋጦው እሳት ውስጥ ምን እንደ ተናገረው ከሙሴ መጽሐፍ አላነበባችሁምን? ይኸውም ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤’ ያለው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር፦ እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 12:26
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እኔ የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ነኝ፤ አት​ፍራ፤ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስለ አባ​ትህ ስለ አብ​ር​ሃም ዘር​ህን አበ​ዛ​ዋ​ለሁ።”


እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ ቆሞ​በት ነበር፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ አት​ፍራ፥ ይህ​ችን አንተ የተ​ኛ​ህ​ባ​ትን ምድር ለአ​ን​ተም ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለሁ፤


የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም ፍር​ሀት ከእኔ ጋር ባይ​ሆ​ንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰ​ደ​ድ​ኸኝ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዋ​ረ​ዴ​ንና የእ​ጆ​ችን ድካም አየ፤ ትና​ን​ትም ገሠ​ጸህ።”


ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ሆይ፥ የአ​ባቴ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድ​ርህ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​በ​ትም ስፍራ ተመ​ለስ፤ በጎ​ነ​ት​ንም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ’ ያል​ኸኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥


በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን አቆመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ጠራ።


ሂድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰብ​ስብ፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፦ መጐ​ብ​ኘ​ትን ጐበ​ኘ​ኋ​ችሁ፤ በግ​ብ​ፅም የሚ​ደ​ረ​ግ​ባ​ች​ሁን አየሁ፤


‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?”


ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡምም።


ሙታን እን​ደ​ሚ​ነ​ሡስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ‘እኔ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ’ ብሎ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ዘንድ እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው ሙሴ ተና​ግ​ሮ​አል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ን​ኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላ​ረ​ግ​ሁ​ምና፤ ነገር ግን ወደ ወን​ድ​ሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አም​ላኬ፥ ወደ አም​ላ​ካ​ች​ሁም አር​ጋ​ለሁ አለ ብለሽ ንገ​ሪ​አ​ቸው” አላት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ውን ሕዝ​ቡን አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያስ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በከ​ሰ​ሳ​ቸው ጊዜ መጽ​ሐፍ ያለ​ውን አታ​ው​ቁ​ምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች