Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በል​ቡ​ና​ቸው የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና አንድ ሕፃን ወስዶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አቆ​መው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ኢየሱስም የልባቸውን ሐሳብ ተረድቶ፣ አንድ ሕፃን ይዞ በአጠገቡ አቆመ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ኢየሱስም የልባቸውን አሳብ አውቆ አንድ ሕፃን ወሰደና፥ በአጠገቡም አቁሞት፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ኢየሱስ ግን የልባቸውን ሐሳብ ዐውቆ አንድ ሕፃን ልጅ አመጣና በአጠገቡ አቆመው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ኢየሱስም የልባቸውን አሳብ አውቆ ሕፃንን ያዘ፤ በአጠገቡም አቁሞ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:47
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁን አንተ ሁሉን እን​ደ​ም​ታ​ውቅ፥ ማንም ሊነ​ግ​ርህ እን​ደ​ማ​ትሻ ዐወ​ቅን፤ በዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣህ እና​ም​ና​ለን።”


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በል​ባ​ችሁ ምን ታስ​ባ​ላ​ችሁ?


ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሁሉ እንደ መን​ገ​ዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመ​ረ​ም​ራ​ለሁ፤ ኵላ​ሊ​ት​ንም እፈ​ት​ና​ለሁ።”


ሁል​ጊዜ በል​ባ​ቸው ዐመ​ፃን የሚ​መ​ክሩ፥ ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ ይከ​ብ​ቡ​ኛል።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።


ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


የሰ​ው​ንም ግብ​ሩን ሊነ​ግ​ሩት አይ​ሻም፤ እርሱ በሰው ያለ​ውን ያውቅ ነበ​ርና።


ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ሁሉንም ፈወሳቸው፤ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች