Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ከደ​መ​ና​ውም ውስጥ፥ “የመ​ረ​ጥ​ሁት ልጄ ይህ ነው፤ እር​ሱን ስሙት” የሚል ቃል መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከደመናውም ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ከደመናውም፦ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ከደመናውም ውስጥ፥ “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:35
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መን​ፈስ ቅዱ​ስም የር​ግብ መልክ ባለው አካል አም​ሳል በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰ​ማ​ይም፥ “የም​ወ​ድህ፥ በአ​ን​ተም ደስ የሚ​ለኝ ልጄ አንተ ነህ” የሚል ቃል መጣ። ሉቃ. 9፥35።


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


ከተ​ፈ​ጸ​መም በኋላ ለሚ​ታ​ዘ​ዝ​ለት ሁሉ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኅን ሆነ።


“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ እነ​ዚያ እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ” ብሎ​አ​ልና።


እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ድያ ልጁን ቤዛ አድ​ርጎ እስ​ኪ​ሰጥ ድረስ ዓለ​ሙን እን​ዲህ ወዶ​ታ​ልና።


“እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።


በአንተ ደስ ይለኛል፤” የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።


ይህ​ንም ሲና​ገር ደመና መጣና ጋረ​ዳ​ቸው፤ ወደ ደመ​ና​ውም በገቡ ጊዜ ፈሩ።


አባት ሆይ፥ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው።” ከሰ​ማ​ይም፥ “አከ​በ​ር​ሁህ፤ ደግ​ሞም እን​ደ​ገና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤” የሚል ቃል መጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች