Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ማን ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው፤ ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሲሕ ነህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እርሱም፣ “እናንተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም፣ “አንተ የእግዚአብሔር ክርስቶስ ነህ” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እርሱም፦ “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ “የእግዚአብሔር መሢሕ ነህ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እናንተስ፥ “እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ ጴጥሮስም፥ “አንተ የእግዚአብሔር መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:20
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ክር​ስ​ቶስ ነው” ያሉም አሉ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አሉ፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ ከገ​ሊላ ይወ​ጣ​ልን?


“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?”


ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥ እየ​ተ​ረ​ጐ​መና እየ​አ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፥ “ይህ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው” ይል ነበር።


ሳውል ግን እየ​በ​ረታ ሔደ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ለነ​በ​ሩት አይ​ሁድ ይህ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ እያ​ስ​ረዳ መልስ አሳ​ጣ​ቸው።


ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።


እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ እኔ አም​ና​ለሁ” አለ​ችው።


ሴቲ​ቱ​ንም፥ “እኛ ራሳ​ችን ይህ በእ​ው​ነት የዓ​ለም መድ​ኀ​ኒት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ሰም​ተ​ንና ተረ​ድ​ተን ነው እንጂ በአ​ንቺ ቃል ያመ​ን​በት አይ​ደ​ለም” አሏት።


ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው።


ከዮ​ሐ​ንስ ዘንድ ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከተ​ከ​ተ​ሉት ከሁ​ለ​ቱም አንዱ የስ​ም​ዖን ጴጥ​ሮስ ወን​ድም እን​ድ​ር​ያስ ነበር።


“እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ ነህ፤” ብሎ መለሰለት።


ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።


በመ​ን​ገድ ሲሄ​ዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠ​መ​ቅን ምን ይከ​ለ​ክ​ለ​ኛል?” አለው።


“አንተ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ በግ​ልጥ ንገ​ረን” አሉት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብነ​ግ​ራ​ች​ሁም አታ​ም​ኑ​ኝም።


እርሱ ግን ዝም አለ፤ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና “የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን?” አለው።


ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ነው የሚ​ሉህ አሉ፤ ኤል​ያስ ነው የሚ​ሉ​ህም አሉ፤ ከቀ​ደ​ሙት ነቢ​ያት አንዱ ተነ​ሥ​ቶ​አል የሚ​ሉ​ህም አሉ” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች