Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ቀኑም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት መጥ​ተው፥ “ያለ​ን​በት ምድረ በዳ ነውና በዙ​ሪ​ያ​ችን ወዳሉ መን​ደ​ሮ​ችና ገጠ​ሮች ሄደው እን​ዲ​ያ​ድሩ የሚ​በ​ሉ​ት​ንም እን​ዲ​ያ​ገኙ ሕዝ​ቡን አሰ​ና​ብት” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ቀኑም ሊመሽ ሲል፣ ዐሥራ ሁለቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ያለነው በምድረ በዳ ስለ ሆነ፣ ሕዝቡ ወደ አካባቢው መንደርና ገጠር ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ቀኑም ይመሽ ጀመር፤ ዐሥራ ሁለቱም ቀርበው፦ “በዚህ በምድረ በዳ ስላለን በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩና ምግብ እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ቀኑ ሊመሽ ሲል፥ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ይህ ያለንበት ቦታ በረሓ ነው፤ ስለዚህ ሰዎቹ በአካባቢው ወዳሉት ከተሞችና ገጠሮች ሄደው ምግብና ማደሪያ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ቀኑም ይመሽ ጀመር፤ አሥራ ሁለቱም ቀርበው፦ በዚህ በምድረ በዳ ነንና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩና ምግብ እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:12
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የሰ​ላ​ም​ንም ቃል ኪዳን ከዳ​ዊት ቤት ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድር አጠ​ፋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም በም​ድረ በዳ ይኖ​ራሉ፤ በዱ​ርም ውስጥ ይተ​ኛሉ።


በም​ድረ በዳና በዞ​ር​ህ​በት ምድር ሁሉ ጠበ​ቅ​ሁህ።


ኢየሱስም በሰማ ጊዜ ከዚያ ብቻውን ወደ ምድረ በዳ በታንኳ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡም ሰምተው ከከተማዎቹ በእግር ተከተሉት።


እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት፤” እያሉ ለመኑት።


ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ “ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም፤” አላቸው።


ሕዝ​ቡም ዐው​ቀው ተከ​ተ​ሉት፤ እር​ሱም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትም አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ሊፈ​ወሱ የሚ​ሹ​ት​ንም አዳ​ና​ቸው።


እርሱ ግን፥ “እና​ንተ የሚ​በ​ሉ​ትን ስጡ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚ​በቃ ምግብ ልን​ገዛ ካል​ሄ​ድን ከአ​ም​ስት እን​ጀ​ራና ከሁ​ለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለ​ንም” አሉት።


ከዚህ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ሄደ።


እኔም ይህቺ ሥራ በጸ​ሎ​ታ​ች​ሁና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ወደ ሕይ​ወት እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ሰኝ አው​ቃ​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች