ሉቃስ 8:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)45 ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማን ዳሰሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩትም፥ “መምህር ሆይ፥ ሰው ይጋፋህና ያጨናንቅህ የለምን? አንተ ግን ማን ዳሰሰኝ? ትላለህ” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም45 ኢየሱስም፣ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም መንካታቸውን በካዱ ጊዜ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ ሕዝቡ ሁሉ ከብቦህ በግፊያ እያስጨነቀህ ነው” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)45 ኢየሱስም፦ “ማን ነው የነካኝ?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስ፦ “አቤቱ! ሕዝቡ በዙሪያህ ከበውህ እየተጋፉህ እኮ ነው!” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም45 ኢየሱስም “ማን ነው የነካኝ?” ሲል ጠየቀ። ሁሉም “እኛ አልነካንህም፤” አሉ፤ ጴጥሮስም “መምህር ሆይ፥ ሕዝቡ እየተጋፋ ሲከተልህ እያየህ ማን ነው የነካኝ ትላለህን?” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)45 ኢየሱስም፦ የዳሰሰኝ ማን ነው? አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩት፦ አቤቱ፥ ሕዝቡ ያጫንቁሃልና ያጋፉህማል፤ የዳሰሰኝ ማን ነው ትላለህን? አሉ። ምዕራፉን ተመልከት |