Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እነ​ሆም ኢያ​ኢ​ሮስ የሚ​ባል ሰው መጣ፤ እር​ሱም የም​ኵ​ራብ ሹም ነበር፤ ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር በታ​ችም ሰገደ። ወደ ቤቱም ይገባ ዘንድ ለመ​ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 በዚህ ጊዜ ኢያኢሮስ የተባለ የምኵራብ አለቃ መጥቶ፣ በኢየሱስ እግር ላይ በመውደቅ ወደ ቤቱ እንዲሄድለት ለመነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እነሆም፥ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው መጣ፤ እርሱም የምኵራብ አለቃ ነበረ፤ በኢየሱስም እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ለመነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 በዚያን ጊዜ አንድ የምኲራብ አለቃ የሆነ፥ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው መጣ፤ በኢየሱስ እግር ሥር ወድቆ፥ “እባክህ ወደ ቤቴ ናልኝ፤” ብሎ ለመነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እነሆም፥ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው መጣ፥ እርሱም የምኵራብ አለቃ ነበረ በኢየሱስም እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ለመነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:41
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የም​ኵ​ራብ አለቃ ቀር​ስ​ጶ​ስም ከነ​ቤተ ሰቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አመነ፤ ከቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎ​ችም ብዙ​ዎች ሰም​ተው አም​ነው ተጠ​መቁ።


ኦሪ​ት​ንና ነቢ​ያ​ትን ካነ​በቡ በኋ​ላም የም​ኵ​ራቡ አለ​ቆች፥ “እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለሕ​ዝብ ሊነ​ገር የሚ​ገ​ባው የም​ክር ቃል እንደ አላ​ችሁ ተና​ገሩ” ብለው ላኩ​ባ​ቸው።


የም​ኵ​ራቡ ሹምም ጌታ ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ፈው​ሶ​አ​ልና፤ እየ​ተ​ቈጣ መልሶ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሥራ​ች​ሁን የም​ት​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ስድ​ስት ቀኖች ያሉ አይ​ደ​ለ​ምን? ያን​ጊዜ ኑና ተፈ​ወሱ፤ በሰ​ን​በት ቀን ግን አይ​ሆ​ንም።”


ይህ​ንም ሲና​ገር አንድ ሰው ከም​ኵ​ራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅ​ህስ ሞታ​ለች እን​ግ​ዲህ መም​ህ​ሩን አታ​ድ​ክ​መው” አለው።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።


አረ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ የም​ኵ​ራ​ቡን አለቃ ሶስ​ቴ​ን​ስን ይዘው በሸ​ንጎ ፊት ደበ​ደ​ቡት፤ የእ​ር​ሱም ነገር ጋል​ዮ​ስን ምንም አላ​ሳ​ዘ​ነ​ውም።


ልዳም ለኢ​ዮጴ ቅርብ ነበ​ርና ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጴጥ​ሮስ በዚያ እን​ዳለ ሰም​ተው ወደ እነ​ርሱ መም​ጣት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ ይማ​ል​ዱት ዘንድ ሁለት ሰዎ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።


በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ሰው​የ​ውም ሳም​ራዊ ነበር።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር።


ዕድ​ሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚ​ሆ​ናት አን​ዲት ልጅ ነበ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም ልት​ሞት ቀርባ ነበ​ረች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች