Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ጋኔን ያደ​ረ​በት ሰው ከከ​ተማ ወጥቶ ተገ​ና​ኘው፤ ልብ​ሱ​ንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመ​ቃ​ብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይ​ገ​ባም ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ፣ አጋንንት ያደረበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ አገኘው፤ ይህ ሰው ለብዙ ጊዜ ልብስ ሳይለብስ፣ በቤትም ሳይኖር በመቃብር ቦታ ይኖር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱም ወደ ምድር እንደ ወረደ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ለረጅም ጊዜ ልብስ አይለብስም ነበር፥ በመቃብሮች እንጂ በቤት ውስጥም አይኖርም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኢየሱስ ከጀልባ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ይህ ሰው ልብሱን ከጣለ ብዙ ጊዜው ነበር፤ የሚኖረውም በመቃብር ቦታ እንጂ በቤት ውስጥ አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ወደ ምድርም በወጣ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፥ ከብዙ ዘመንም ጀምሮ ልብስ ሳይለብስ በመቃብር እንጂ በቤት አይኖርም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:27
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ቃ​ብ​ርም መካ​ከል የሚ​ተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚ​ያ​ልሙ፥ የእ​ሪያ ሥጋም የሚ​በሉ ናቸው። የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደምና ዕቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያረ​ክ​ሳሉ።


በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


ወደ ኢየሱስም መጡ፤ አጋንንትም ያደሩበትን ሌጌዎንም የነበረበትን ሰው ተቀምጦ ለብሶም ልቡም ተመልሶ አዩና ፈሩ።


ከዚህ በኋላ በገ​ሊላ ወደብ አቅ​ጣጫ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ኖን ሀገር በታ​ንኳ ሄዱ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገ​ደ​ለት፤ “የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያ​ለም በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ እን​ዳ​ያ​ሠ​ቃ​የ​ውም ማለ​ደው።


ልብ​ሱ​ንም አወ​ለቀ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ፤ ራቁ​ቱ​ንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ ተጋ​ደመ። ስለ​ዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት መካ​ከል ነውን?” ይባ​ባሉ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች